መግለጫ
ዲጂታል ኢኮኖሚ ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚ ልማት እና እድገት ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ኢትዮጵያ ለፈጣን እና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት እየጣረች እንደመሆኗ መጠን ዲጂታል ኢኮኖሚ ለአገሪቷ ቀጣይ ደረጃ ኢኮኖሚያዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደርጋል። ይህ የዲጂታል ኢኮኖሚ የሸቀጦች እና አገልግሎቶች ንግድ እንዲሁም የክፍያ ስርዓቱን በኢንተርኔት እና በዲጂታል ሲስተም ለመጠቀም ያስችላል። ይህ የሰው ሃይል፣ ሃርድዌር እና የሶፍትዌር መሠረተ ልማት ግንባታን በእጅጉ ይጠይቃል። በዚህ ረገድ የኢትራንሴሽን አዋጁን ማስተዋወቅ ትልቅ የእድገት እርምጃ ተደርጎ ይወሰዳል...